+251 911 989332 ገተር ህንፃ (302B)፡ ራስ ደስታ አካባቢ ፡ አርበኞች መንገድ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ
To English

ዌብ ራሽ ስለየድህረ-ገጽ ቀረፃ ወሬዎች

የድህረ-ገጽ ቀረፃ እና ማደራጀት ስራ ለኢትዮጵያ

ዋጋ ንገረኝ
ለመቀራረብ
ድህረ ገጽ ያስፈልገኝ ይሆን?


ሌሎች ርዕሶች
የድህረ ገጽ ቀረጻ የሚሠራሎች ድርጅት እንዴት መምረጥ ይችላሉ
በ Susan Baroncini-Moe
ትርጉም በዌብ ራሽ
ከ http://www.lifehack.org

የድህረ ገጽ ቀረጻ የሚሠራሎች ድርጅት እንዴት መምረጥ ይችላሉ

በሱዛይ ባሮቺኒ ሞይ ተጽሮ ወደ አማርኛ በፍትህ አለባቸው የተተረጎመ www.lifehack.org)

ምን ያህል ግዜ ሰዎች ድህረ-ገጽ እንሰራላቹሃለን ተብለው ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ ከሚጠበቀው በታች የሆነ ድህረ-ገጽ ይዘው ሲቀሩ ፡ ከዛም ሲያልፍ ገንዘባቸው ቀልጦ ሲቀር ሰምታችኋል? ወይንም አዲስ ጀማሪዋ ባለድርጅት የእህት ወይንም የወንድማችን ልጅ ፡ ወይንም የእራሷን ልጅ በነፃ ድህረ-ገጽ እንዲሰሩላት ካስማማች በኋላ ለማይረባው ስራ አስተያየት ለመስጠት ይሉኝታ ይዟት እሷ ያሰበችውን ሳይሆን የተሰጣትን ድህረ-ገጽ ያዛ ስትቀር ስንቴ ተመልክታችኋል?

አንስተኝ ድርጅቶችን አማካሪ ሆኜ እንደ መስራቴ እነዚህ ታሪኮች በተደጋጋሚ ሰምቻለሁኝ ። በዚህም አንዳዴ ልቤ ሲሰበር ፤ አንዳዴ ስበሳጭ ፡ እንደደንበኞቼ ሆኜ ስቃጠል ቆይቻለሁ ፡ በባለሞያ መፍትሄ አፈላልጌ እስካቀርብላቸው እና ችግሩን እስክንፈታው ድረስ ። በዚህም ምክንያት ተከታታይ አራት ጽሁፎች የፃፍኩኝ ሲሆን ፡ ይህኛው እንዴት ተገቢውን የድህረ-ገጽ ሠራተኛ ድርጅት መቅጠር እንደሚችሉ ይመክራል።

ድህረ-ገጽ የሚሠራሎትን ድርጅት ሲቀጥሩ ለፍተው ያመጡትን ገንዘብ እንዴት እና ለማን መክፈል እንዳለቦት ለማወቅ ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ እና ምን ምን ማሟላት እንዳለባቸው ማወቅ ይጠበቅቦታል። ከዚህ ቀጥሎ አንዳንድ መጠየቅ ያለቦችን ጥያቄዎች ፡ ሠራተኛው ምን ማሟላት እንዳለበት ፡ እንዲሁም ከምን ዓይነት ሠራተኞች መጠንቀቅ እንዳለቦት አስነብባለሁ።

ምን ማሟላት : አለበት እውነተኛ ድርጅት

ድህረ-ገጽ ቀረጻውን የሚሠራሎች ድርጅት የእውነት ስራዬ ብሎ የተቋቋመ መሆኑን ያረጋግጡ ። ይህም ማለት በጣም ትልቅ እና ብዙ ተቀጣሪዎችን የያዘ ድርጅች ብቻ ላይ ያተኩሩ ማለት ሳይሆን በቤተሰቦ ስላወቁት ብቻ ፣ ወይንም ጓደኛዎ ስለሆነ ብቻ ፣ ወይንም ከሱ ጋር እሁድ ቤተ ክርስቲያን ስለሚገናኙ ብቻ መቅጠር የለቦትም ። የሥራ ግንኙነት ከድህረ-ገጽ ሰሪ ቡድኑ ጋር የሚያስፈልግበት በርካታ ምክንያቶች አሉ እነሱም ፦ ያለ ይሉኝቻ በዋጋ ላይ እንዲደራደሩ ፣ እውነተኛ የሆኑ አስተያየቶችን እንዲያቀርቡ ፣ ደስተኛ ያልሆኑባቸው ነገሮች ካሉ በግልፅ ለመነጋገር ስለሚረዳዎት ነው።
ካለምንም ማወላዳት ከዚህ በፊት የሰሩላቸውን ድርጅቶች አድራሻ ይዘው ፡ ከእነዚህ ሰዎች ጋራ መስራት ምን እንደሚመስል ደውለው ይጠይቁ ።

ምን ማሟላት: ድህረ-ገጽ ምን ማሟላት አለባት

ድህረ-ገጽ የሚሰራሎት ድርጅት የራሱ የሆነ ምርጥ ድህረ-ገጽ ሊኖረው ይገባል ። አቀራረጹ የግድ እርሶ የሚወዱት መሆን የለበትም ፡ ነገር ግን የተሟላ መሆን ግን አለበት ። የደንበኞችን ድህረ-ገጽ በመስራት ተጠምጄ የራሴን አልቀረጽኩም የሚለው ምክንያት ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም ። ምርጥ የሆነ ድህረ-ገጽ ለሥራ አስፈላጊ መሆኑን የማያውቁ ከሆነ ፡ ምናልባት ድህረ-ገጽ መስራት ቢያቆሙ ይሻላል።

ከዚህም በተጨማሪ ቀድሞ የሰሯቸውን ድሀረ-ገጾች ዝርዝር ይዘው ቢቃኟቸው የሚመረጥ ሲሆን ፡ የመረጡት ድርጅት ድህረ-ገጽ ላይ ዝርዝሩ በቀላሉ ሊያገኙት ይገባል ። አብዛኞቹ የቀድሞ ስራዎች አሁንም ያሉ መሆን ያለባቸው ቢሆንም አንዳንድ የተቀየሩ ፡ ወይንም የተዘጉ ድህረ-ገጾች ስለማይጠፉ የድህረ-ገጽ ቀራጩ ጥፋት አድርገው አይውሰዱት ። ከአለው የኢኮኖሚ ሁናቴ አኳያ ብዙ ስራዎች ይከፈታሉ ብዙዎችም ይዘጋሉ ። በተጨማሪም የድህረ-ገጽ አቀራረጻቸው ቶሎ ቶሎ የሚቀየር በመሆኑ ፡ አንዳንዶቹ አዲስ የድህረ-ገጽ ቀረጻቸውን አዲስ ድርጅት እንዲሰራላቸው ይቀጥራሉ ፡ አንዳዶቹ ደግሞ ከቀድሞው ጋራ ይቀጥላሉ ።

ምን ጥያዌ ይጠይቃሉ ፡ ድህረ-ገጼ ምን ምን ነገሮችን ማካተት ይኖርበታል?

ይህንን ጥያቄ እንደጠየቁ ፡ መልሶ ስለድርጆቶ ሳይጠይቅ መልስ መስጠት ከጀመረ ፡ እንደ ማስጠንቀቂያ ደወል ቆጥረው ሌላ ድርጅት ቢፈልጉ ይመረጣል ። በጠቅላላው ሲታይ በየድህረ-ገጹ ላይ የማይጠፉ አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩም አንኳን ፡ ድህረ-ገጽ በጥንቃቄ የሚሰራ ድርጅት የእርሶ ጅርጅት ምን እንደሚሰራ ሳያውቅ ፡ የትኛው ስራ ላይ እንደተሰማሩ ሳያውቅ ፡ እንዲሁም ድህረ-ገጾ ምን እንዲሰራሎች እንደሚፈልጉ ሳያውቅ መልስ መስጠት የለበትም ።

ምን ጥያዌ ይጠይቃሉ : ድህረ-ገጼን የምትሰራልኝ ከሀ ጀምረህ ነው ወይንስ ቴምፕሌት (ቀድሞ የተሰራ ዲዛይን ማለት ነው) ትጠቀማለህ?

ጠንካራ የድህረ-ገጽ ቀራጭ ድርጅት ለእርሶ የሚሆን ድህረ-ገጽ ከሀ ጀምሮ ይሰራሎታል ። ሁሉንም ድህረ-ገጽ የሚመሳሰል ቀረጻ አይጠቀምም ፣ ወይንም ቴፕሌት ተጠቅሞ አይሰራሎትም ። የሚሰሩበት ዋጋ ከሃያ አምስት ሺህ ብር በታች ከሆነ በአብዛኛው ጊዜ ለእርሶ ብቻ ተብሎ የሚወጣ አዲስ የድህረ-ገጽ የሚቀርጽሎት አያገኙም ፡ ምንም እንኳን እውነታው ይሄ ቢሆንም በጣም ውድ ዋጋ አስከፍለው ቀድሞ የተሰራ ቴምፕሌት የሚያቀርቡም አጋጥመውኛል ።

ቴፕሌት ለምን መጥፎ ነው? ድህረ-ገጾ ከሌላው ተለይቶ የሚታይ እና አዲስነቱ የሚያስታውቅ መሆን አለበት ። ድህረ-ገጽ መቀረጽ ያለበት የተቋሞን ምልክት ለማንፀባረቅ መሆን ይኖርበታል ። ሲያስቡት ቴምፕሌት ላይ የተመሠረተ ድህረ-ገጽ ምን ያህል ምልክቶን ሊያንፀባርቅ ይችላል ሌላው ሁሉ ድርጅት በቴፕሌት ላይ የተመሠረተ ድህረ-ገጽ ኖሮት ሳለ? በብልጠት የሚያወጡት ወጪ ሁሌም ምክንያታዊ ነው ፡ ለድርጅቶች ደግሞ ምክሬ ፡ ከላይ የገለጽኳቸውን ነገሮች የያዘ ድህረ-ገጽ ከመሆኑ ተጨማሪ ምልክቶን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ፡ ያወጡትን ወጪ የሚያስመልስ ድህረ-ገጽ ይሆናል ።

ምን ጥያዌ ይጠይቃሉ ፡ ድህረ-ገጼ ላይ ለፍለጋ መረቦች የሚጠቅሙ ነገሮችን እንዴት ማካተት ትችላለህ?

ይህንን ጥያቄ ሲጠይቁ መልሱ ስለ ቃላት አጠቃቀም እና “ሜታ ታግ” ብቻ ከሆነ መልሱ ሌላው የቀይ መብራት ነው ወደ ሌላ ድርጅት ፍለጋዎ ይሰማሩ ። የድህረ-ገጽ ቀራጭ ድርጅት ስለስራው በቁም ነገር የሚያስብ ከሆነ ስለ ፍለጋ መረቦች ከድህረ-ገጽ ጋር ማዋሃድ በቂ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ፕሮግራሚንጉ ላይ ምን መጨመር አለበት ፣ ግልባጩ ላይስ ፣ በጠቅላላው ድህረ-ገጽ ላይስ ምን ይደረግ የሚለውን ማወቅ አለበት።

መልስ ሲሰጥዎች “ፍላሽ” እጠቀማለሁ የሚሉ ከሆነ ፡ ይህንን መጠቀም ድህረ-ገጼ ላይ ምን ችግር ያስከትላል ፡ ድህረ-ገጼን የፍለጋ መረቦቹ ለመመዝገብ ችግር አይፈጥርባቸውም ወይ ብለው ይጠይቁ ። ምን አይነት መልስ እንደሚሰጥዎት ያስተውሉ ፡ ትክክለኛው መልስ ጥልቀት ያለው እና ትንሽ የሚያምታታ ቢሆንም መልሳቸው ግን “ፍላሽ” “ጉግል” ላይ ችግር አይፈጥርም መሆን የለበትም።

ምን ጥያዌ ይጠይቃሉ : ከንግድ አማካሪዎች ጋራ አብረው ይሰራሉ ወይስ ድርጅቶ ይህንን አይነት አገልግሎች ለአነስተኛ ተቋማት ይሰጣል?

በጣም ምርጥ የተባሉት የድህረ-ገጽ ድርጅቶች ሰራተኞቻቸው መካከል የንግድ ሥራ አማካሪ ይኖራቸዋል ፡ወይንም ከአነስተኛ የንግድ ሥራ አማካሪ ድርጅቶች ጋራ ግንኙነት ይኖራቸዋል ፤ እነዚህም አማካሪዎች ከዚህ በፊት ያልተሰራበት የንግድን ሃሳብ እንዴት ማጎልበት እንደሚቻል ከደንበኞች ጋራ መመካከር የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ።

ማስጠንቀቂያ ፡ የማይረቡ አማካሪዎች ጋር በመሄዶ የሚያተርፉት ነገር ቢኖር የጠራውን ውሃ ሲያደፈርሱት መመልከት ሲሆን ፣ የንግድ ስራዎችን በሚገባ ከማወቁም በላይ የቴክኒክ ቃላትን በሚገባ የሚረዳ አማካሪ ጋር ቢሄዱ ደግሞ በእርሶ እና በድህረ-ገጽ ቀራጩ መሀከል ሊኖር የሚችለው ክፍተት ከመሙላቱም በላይ ፤ የሚያስፈልገውን የመግባባት መንገድ ክፍት ያደርገዋል ፡ ከዚህም ሂደት በመጨረሻ የሚገኘው ድህረ-ገጽ በጣም ጥሩ እና ጠቃሚ ያመቻችሎታል ።

ድህረ-ገጽ ከሚሰሩሎት ድርጅቶች ጋር ከመነጋገሮ በፊት የንግድ አማካሪ ፈልገው ለመግኘት ይሞክሩ ። ጥሩ የሆነ የንግድ አማካሪ ከድህረ-ገጽ ቀራጮች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል ፡ ከዚህ በፊትም ያሰራቸው ስራም ሊኖር ይችላል ። በዚህም መንገድ የንግድ አማካሪዎ ጋር የሰራውን ድርጅት ከማግኘቶም በላይ ፡ በአማካሪዎም በኩል ጥሩ የሆነ የዋጋ ድርድር ማግኘት ይችላሉ ።

ምን ምን መመልከት አለቦት ፡ ዋጋ አወጣጥ

እንደየትኛውም የስራ ዓይነት በጣም ውድ ዋጋ የሚያስከፍሉ ድርጅቶች እንዳሉ ሁሉ ዋጋቸውንም ጥለው ለመወዳደር የሚሞክሩ ድርጅቶችም አሉ ። የእርሶ ፈተና የሆነው ተመጣጣኙን ዋጋ ማወቅ ነው።

በርካታ ባለሙያዎች ድህረ-ገጽን ውጭ ሃገር ሆነው በርካሽ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በጣም በጣም በርካሽ ማሰራት ይቻላል ብለው ይመክራሉ። ምንም እንኳን ይሄ አሰራር ጠቃሚ የሚሆንበት ግዜ ቢኖርም ጥንቃቄ ግን ማድረግ ያስፈልጋል። በርካታ በግልጽ የማይታዩ ወጪዎች ተያይዘው ሊመጡቦት ይችላል።

አንደኛ ፡ በእርግጠኝነት ከማን ጋራ እንደሚሰሩ ካላወቁ እና እነዚህም ሰዎች አስተማማኝ ካልሆኑ ፡ ገንዘቦን እንዲሁም ጠቃሚ የሆነ የግል መረጃዎን ለማይታወቁ ሰዎች እየሰጡ መሆኑን ያስተውሉ።

ሁለተኛ ፡ ከውጭ ሀገር ቀራጮች ጋር በሚሰሩበት ግዜ ትልቅ የሆነ የቋንቋ ክፍተት ሊኖር ይችላል ፡የዚህም ውጤት ለሚሰሩት ድህረ-ገጽ ትልቅ የሆነ ውድቀት ሊፈጥር ይችላል ።እዚህ ጋር ልናገር የፈለኩት በመጥፎ አትተርጉሙብኝ ።

በጣም ምርጥ የሆኑ የድህረ-ገጽ ቀራጮችን ከሌላ ሃገር ማግኘት ይችላሉ ፡ ነገር ግን እነሱን በሚፈልጉበት ወቅት በርካታ የማይረብ ድርጅቶችም ያጋጥሞታል ።

ምን ጥያዌ ይጠይቃሉ ፡ ድህረ-ገጼን በይዘት አስተዳደር ሊሰሩልኝ ይችላሉ?

ድህረ-ገጾን እራሶ የማስተዳደር ስራ ለመስራት ካሰቡ ፡ HTML ወይንም Dreamweaver ሳይማሩ ድህረ-ገጽ ቀራጮን በይዘት ማስተዳደሪያ ሲስተም እንደሚሰሩ ይጠይቋቸው ። በዚህም አሰራር የእራሶን ድህረ-ገጽ ማስተዳደር ይችላሉ ፡ ፎቶዎችን መጨመር ፡ ተጨማሪ ገልፆችን መጨመር ወይንም መቀነስ ይችላሉ ፡ ይህንንም ለማድረግ ከየትኛውም የአለም ክፍል ሆነው መተግበር ይችላሉ።

ከሁሉም በላይ ማወቅ የሚገባዎት ነገር

ድህረ-ገጽ ቀራጭ ድርጅቱ ውስጥ ከእርሶ ጋር የሚነጋገረው ሰው የእርሶን የንግድ ቋንቋ በሚገባ ከመረዳቱም በላይ ከፕሮግራመሮቹም ጋር በቀላሉ መግባባት የሚችል መሆን ይኖርበታል ። የሚያገኙት ሰው የሚያነጋግሮት በጥራዝ ነጠቅነት ሳይሆን የድህረ-ገጽ ነገሮችን እና አሰራሮችን በሚገባ ሊገልፅሎት የሚችል መሆን አለበት ። የደንበኞች አገልግሎት በጣም ወሳኝ በመሆኑ ኢሜሎንም ሆነ የስልክ ጥሪዎን በተገቢው ፍጥነት የሚመልስ ሰው እንደሆነ ማረጋገጥ ይኖርቦታል።

መርሳት የሌለቦት ነገር ቢኖር ፡ ምንም እንኳን የድህረ-ገጽ ቀረፃው በድህረ-ገጽ ቀራጩ ትከሻ ላይ የወደቀ ቢሆንም እርሶም ቢሆኑ ሃላፊነት እንዳለቦት ነው።

ኢንተርኔትን እና google classroom በመጠቀም እንዴት ማስተማር ይቻላል

በፍትህ አለባቸው ከweb-rush.com የቀረበ

ኢንተርኔትን በመጠቀም ትምህርት ማስተማር በብዙ መልኩ ሊከናወን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፤ እኔ ግን የሞከርኩት የgoogle ስሪት የሆነውን classroom.google.com ን ነው። ለታብሌት እና ለሞባይል ተጠቃሚዎች app ስላለው በሱም መጠቀም ይችላሉ።

እንዴት እንደሚጠቀሙ ለትምህርት ቤቶች(አስተማሪዎችና) ለተማሪዎች ብዬ ከፋፍዬ አቀርቤዋለሁ።

ለትምህርት ቤቶች ወይም ለአስተማሪዎች (የgoogle ወይንም gmail አድራሻ ካሎት ከተራ ቁጥር 3 ጀምሮ እስከ ተራ ቁጥር ድረስ 13 ማንበብ አያስፈልጎትም)

ለተማሪዎች
(የgoogle ወይንም gmail አድራሻ ካሎት ከተራ ቁጥር 3 ካነበቡ በኋላ ወደ ተራቁጥር 14 ይሂዱ)

Give Me Price Quote

want to talk about websites?

As a website developer the answer is always yes you do. But to make sure of your organizational need I am preparing a quiz that will help you decide. For now write to me by clicking on In Touch, and I will tell you what I think.